አማርኛ እርዳታ እና እገዛ : የህዝብ ቆጠራዎትን በወረቀት ላይ ስለመሙላት

የህዝብ ቆጠራ መጠይቀ ቅጽ የወረቀት ቅጂ በፖስታ እንዲንልክለዎ ለመጠየቅ፣ በአማርኛ አንድ ሰራተኛ ለማነጋገር ለነፃ የቋንቋ እገዛ መስመራችን በ 0800 587 2021 ላይ ይደውሉ።

Important information:

የህዝብ ቆጠራ መጠይቀ ቅጽዎትን በእንግሊዝኛ መሙላት አለበዎ። ዌልስ ውስጥ የሚኖሩ ከሆነ በዌልሽኛ ሊመልሱ ይችላሉ።

በራስዎ ካልቻሉም፣ የህዝብ ቆጠራውን ሌላ ሰው ሊሞላለዎት ወይም ሊያግዝዎት ይችላል።

የቤተሰብ መጠይቀ ቅጽ መመሪያ አነስተኛ መጻህፍት

የህዝብ ቆጠራዎትን በወረቀት ላይ ለመሙላት ይረዳዎት ዘንድ፣ በአማርኛ የተዘጋጀ አንድ አነስተኛ መጽሀፍ ከድረ-ገጽ ላይ አውርደው ማግኘት ይችላሉ። አንድ ቅጂ በፖስታ እንዲንልክለዎ ለመጠየቅ፣ ለነፃ የቋንቋ እገዛ መስመራችን በ 0800 587 2021 ላይ በመደወል አንድ ሰራተኛ ማነጋገርም ይችላሉ። አነስተኛ መጽሀፉ የያንዳንዳቸውን የህዝብ ቆጠራ ጥያቄዎች ትርጉም እና ስለህዝብ ቆጠራ የበለጠ መረጃ በ አማርኛ ይዟል።

ዌልስ ውስጥ የሚኖሩ ከሆነ፣ ጥያቄ 17 በቤተሰብ መጠይቀ ቅጹ መመሪያ አነስተኛ መጽሀፍ ውስጥ ያልተተረጎመ ተጨማሪ ጥያቄ ነው። ጥያቄ 17ን ለመተርጎም እርዳታ የሚፈልጉ ከሆነ ለነፃው የቋንቋ እርዳታ መስመራችን በ 0800 587 2021 ላይ መደወል ይችላሉ።

Important information:

መልሶችዎትን በመመሪያው አነስተኛ መጽሀፍ ላይ ሳይሆን በህዝብ ቆጠራው የወረቀት ቅጽ ላይ መሙላት አለበዎ።

እርዳታ ከፈለጉ

በአማርኛ ተጨማሪ እርዳታ ለማግኘት ለነፃ የቋንቋ እርዳታ መስጫ መስመራችን በ 0800 587 2021 ላይ ይደውሉ።