አማርኛ እርዳታ እና እገዛ : የህዝብ ቆጠራዎትን በበይነ መረብ ስለመሙላት

የህዝብ ቆጠራዎትን በበይነ መረብ ላይ መሙላት ለመጀመር፣ በላክንልዎ ደበዳቤ ላይ ያስቀመጥንለዎትን ሚስጢራዊ መግቢያ ያስገቡ። ሚስጥራዊው መግቢያ ብዛታቸው16 የሆኑ ሆሂያት እና ቁጥሮችን አደባልቆ የያዘ ነው።

ሚስጥራዊው የመግቢያ ቁልፍ(ኮድ)በደብዳቤው መሃል ላይ መሆኑን የሚያሳይ የህዝብ ቆጠራ  ምሳሌ ደብዳቤ
Warning:

ሚስጥራዊ መግቢያዎትን በጥንቃቄ ይያዙ። የህዝብ ቆጠራዎትን በበይነ መረብ ላይ በሚሞሉበት ጊዜ ሁልዬም ማስገባት ይኖርበዎታል።

Important information:

የህዝብ ቆጠራ መጠይቀ ቅጽዎትን በእንግሊዝኛ መሙላት አለበዎ። ዌልስ ውስጥ የሚኖሩ ከሆነ በዌልሽኛ ሊመልሱ ይችላሉ።

በራስዎ ካልቻሉም፣ የህዝብ ቆጠራውን ሌላ ሰው ሊሞላለዎት ወይም ሊያግዝዎት ይችላል።

የበይነ መረብ ተርጓሚ መሳሪያዎችን የሚጠቀሙ ከሆነ፣ የህዝብ ቆጠራው ጥያቄዎች በትክክል ላይተረጎሙ እንደሚችሉ ልብ ይበሉ።

የህዝብ ቆጠራዎን በበይነ መረብ ላይ ለመሙላት ተዘጋጅተዋል?

Start census

እርዳታ ከፈለጉ

አዲስ ሚስጥራዊ መግቢያ እንዲላክልዎ ለመጠየቅ ወይም በአማርኛ ተጨማሪ እርዳታ ለማግኘት ከፈለጉ ለነፃ የቋንቋ እርዳታ መስጫ መስመራችን 0800 587 2021 ላይ መደወል ይችላሉ።